በምስራቅ አፍሪካ ለትርፍ ያልተቋቋመው የሕክምና ምርምር ድርጅት ችላ ለተባሉ በሽታዎች መድሃኒት ተነሳሽነት (ዲኤንዲአይ) እና አጋሮቹ ባደረጉት ጥናት ምክንያት አጭር እና እምብዛም ከባድ ያልሆነ ህክምና የቪሴራል ሊሽመናይሲስ ላለባቸው ሰዎች ውጤታማ ሆኖ ተገኝቷል። ውጤቶቹ ዛሬ በክሊኒካል ኢንፌክሺየስ ዲዚዝ መጽሔት ላይ ታትሟል.
አዲሱ ሕክምና ሁለት መድኃኒቶችን ማለትም፣ ሚልቴፎሲን (ኤምኤፍ)፣ ለሊሽመናይሲስ ሕክምና የሚሆነው ብቸኛው በአፍ የሚወሰድ መድሐኒት እና በመርፌ የሚሰጥ ፓሮሞማይሲን (ፒኤም) አንቲባዮቲክን ያካትታል።
“ይህ አዲስ ህክምና በክልሉ ውስጥ በቪሴራል ሊሽመናይሲስ ለተጎዱ በሺዎች ለሚቆጠሩ ህሙማን ታላቅ ዜና ነው። ከህክምናው ውስጥ አንድ የሚያሰቃይ እና ከባድ የሆነ መርፌን ያስወግዳል ስለዚህም ለተጎዱት የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ሲሉ በካርቱም ዩኒቨርሲቲ ምክትል ቻንስለር እና በሱዳን የተካሄደው ክሊኒካዊ ሙከራ ዋና መርማሪ ፕሮፌሰር አህመድ ሙሳ ተናግረዋል።”
ሊሽመናይሲስ ከወባ ቀጥሎ በጣም ጥገኛ ገዳይ ነው። በጣም ከባድ የሆነው ቪሴራል ሊሽመናይሲስ (ቪኤል) ካልታከመ ለሞት ይዳርጋል። በዓመት ከ50,000 እስከ 90,000 አዳዲስ በበሽታው የተያዙ ሲኖሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በኤርትራ፣ በኢትዮጵያ፣ በኬንያ፣ በሶማሊያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በሱዳን እና በኡጋንዳ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው። በሽታው በሀብት-ውሱን አካባቢዎች፣ ደረቃማ እና ከፊል ደረቃማ አካባቢዎች ላይ ያሉ ሰዎችን ይጎዳል። ከእነዚህ ውስጥ ግማሾቹ ከ15 አመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው። ሊሽመናይሲስ እንዲሁ በአየር ንብረት መለዋወጥ የሚመጣ በሽታ ነው፣ እና ተጽኖው እየባሰ ሊሄድ ይችላል። ስለዚህ፣ መፍትሄ ካልተሰጠው፣ በጣም የተጋለጡ ሰዎች መሰቃየታቸውን ይቀጥላሉ።
አሁን ያለው የምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ መስመር ህክምና ፓሮሞማይሲን (ፒኤም)፣ ከሶዲየም ስቲቦግሉኮኔት (ኤሴኤስጂ) ጋር በማጣመር በመርፌ የሚሰጥ አንቲባዮቲክ በመርፌም ሆነ በደም ስር የሚሰጥ ነው። ከኤስ.ኤስ.ጂ ጋር በተያያዘ እንደ ካርዲዮቶክሲሲቲ፣ ሄፓቶቶክሲሲቲ እና የፓንክሪያታይተስ በሽታ ባሉ ብዙ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊሰቃዩ ስለሚችሉ አናሳ ሆኖ ይቆያል። ሕመምተኞች በየቀኑ ሁለት የሚያሙ መርፌዎችን ለ17 ቀናት መውሰድስ ስላለባቸው ሕክምናውን ለመሰጠት አስቸጋሪ ነው።
“ህሙማን ለረጅም ጊዜ በሆስፒታል ውስጥ እንዲቆዩ እና ከስራ ወይም ከትምህርት ቤት እንዲቀሩ ስለሚገደዱ አሁን ያለው ህክምና ከፍተኛ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ አለው። በአዲሱ ህክምና ህሙማኖች በሆስፒታል ውስጥ የሚያሳልፉት ጊዜ ያነሰ ይሆናል ሲሉ” ፕሮፌሰር ሙሳ ተናግረዋል
ውጤቱ ዛሬ ይፋ የሆነው እ.ኤ.አ. በ2017 በኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ኡጋንዳ በአፍሪካዲያ ኮንሰርቲየም ከአውሮፓ እና በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ክሊኒካል ሙከራዎች አጋርነት (ኢዲሲቲፒ) በተገኘ እገዛ በመነጨው ክሊኒካዊ ሙከራ ነው። ጥናቱ ለ14 ቀናት የሚሰጠውን ሚልቴፎሲን እና ፓሮሞማይሲን የተባሉ ሁለት መድኃኒቶችን ለ17 ቀናት ከሚሰጡት የሶዲየም ከሶዲየም ስቲቦግሉኮኔት እና ፓሮሞማይሲን የሕክምና ደረጃ ጋር አነጻጽሮታል።
ውጤቶቹ እንደሚያሳዩት የኤሜፍ+ፒኤም ህክምና ቪሴራል ሊሽመናይሲስን ለማከም ከ91% በላይ ውጤታማ ነው። ይህ ህክምና ልክ እንደ ነባሩ ህክምና ውጤታማ ቢሆንም፣ የሆስፒታል ህክምና ጊዜን በ18% በመቀነስ አንድ የሚያሳምም ዕለታዊ መርፌን እና ከሶዲየም ስቲቦግሉኮኔት ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችለውን ለህይወት የሚያሰጋ መርዛምነትን የማስወገድ ጥቅም አለው። ስለዚህ የበለጠ ለታካሚ ተስማሚ ነው። አብዛኞቹ የቪሴራል ሊሽመናይሲስ ሕሙማን የሆኑት ሕፃናት ለዚህ አዲስ ሕክምና ጥሩ ምላሽ እንደሚሰጡ ታይቷል እናም በተለይ በዚህ ሕክምና ተጠቃሚ ይሆናሉ። ሕክምናው በተጨማሪ የድህረ ካላዛር ደርማል ሊሽመናይሲስ (ፒኬዲኤል) – የተለመደ የቪሴራል ሊሽመናይሲስ ችግር በተለይ በሱዳን እና ኢትዮጵያ ውስጥ ከታከመ በኋላ ወደ 4% ይቀንሳል ይህም በኤስኤስጂ+ፒኤም ከታከመው ከ 20.9% ያነሰ ነው። ይህ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም የፒኬዲኤል ህሙማን ለአሸዋ ዝንቦች የኢንፌክሽን ምንጭ ናቸው ፣ ስለሆነም የ ፒኬዲኤል ጉዳዮችን መቀነስ ስርጭቱን ይቀንሳል።
“አዲሱ ጣምራ ህክምና በሚያሳዝን ሁኔታ ችላ ለተባሉ ህሙማኖች ታሪካዊ እርምጃን ያመለክታል። ከበርካታ አሥርተ ዓመታት በኋላ በመጨረሻ በአፍ የሚወሰድ ሕክምናን አካትተናል፣ ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶችን እና በጤና ሥርዓቶች ላይ ያለውን ሸክም በመቀነስ የሆስፒታል ቆይታ ጊዜ በመቀነሱ ምስጋና ይገባው በማለት፣ በናይሮቢ፣ ኬንያ የዲኤንዲአይ የምስራቅ አፍሪካ ክልላዊ ዳይሬክተር ዶክተር ሞኒክ ዋሱና ተናግረዋል።
ህሙማኑ በቅርቡ ህክምናውን ማግኘት እንዲችሉ የጥናት ውጤቱን ለክልሉ ባለድርሻ አካላት በማካፈል አዲሱን ጥምረት ለማመቻቸት ጥረት ተጀምሯል።
“በዚህ ክሊኒካዊ ሙከራ በተገኙት አወንታዊ ውጤቶች ተደስተናል። በ2025 በሊሽመናይሲስ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎችን በ60 በመቶ ለመቀነስ ለስልታዊ ግባችን አስተዋፅዖ ያደርጋል ሲሉ በኬንያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል ዶክተር ፓትሪክ አሞት ተናግረዋል። “የእኔን የቴክኒክ አማካሪ ቡድን በዲኤንዲአይ የቀረቡትን ማስረጃዎች እንዲገመግም እና አዲሱን ህክምና ለመቀበል ምክሮችን እንዲሰጥ ጠይቄያለሁ።”
ዲኤንዲአይ እና አጋሮቹ የመርፌ ፍላጎትን ሙሉ በሙሉ የሚያስወግዱ እና ከአካባቢው ሁኔታ ጋር በተሻለ ሁኔታ የሚስማሙ የተሻሉ ህክምናዎችን ለማግኘት እየሰሩ ነው
“ጉዞው ገና አላለቀም። ዲኤንዲአይ እና አጋሮቹ ለሊሽመናይሲስ አዲስ፣ ተስፋ ሰጭ እና ሁሉም-በአፍ ለሚወሰዱ ህክምናዎች በቅርቡ ክሊኒካዊ ሙከራዎችን ይጀምራሉ ሲሉ የዲኤንዲአይ ችላ የተባሉ የትሮፒካል በሽታዎች ሊሽመናይሲስ እና የማይሴቶማ ክላስተር ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ፋቢያና አልቬስ ተናግረዋል።” “ዓላማችን ለታካሚ ተስማሚ የሆኑ በአፍ የሚወሰዱ ህክምናዎችን በማዘጋጀት ለቪሴራል ሊሽመናይሲስ ህክምናዎችን በከፍተኛ ደረጃ፣ ተመጣጣኝ, ደህንነቱ የተጠበቀ እና በሁሉም ክልሎች ውስጥ ለታካሚዎች ውጤታማ የሆነ ለውጥ ማምጣት ነው።”
ስለ አፍሪካዲያ ኮንሶርቲየም
አፍሪካዲያ በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ የተሻሻሉ ህክምናዎችን እና ለቪሴራል ሊሽመናይሲስ የመመርመሪያ መሳሪያዎችን ለማግኘት የተፈጠረ ማህበር ነው። ባለፉት 12 ዓመታት ውስጥ፣ የአፍሪካዲያ ኮንሰርቲየም አጋሮች በምስራቅ አፍሪካ ክልል ውስጥ አዳዲስ የቪኤል ሙከራዎችን አድርገዋል። ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ የጋራ ጥረቶች ነበሩ። ጥምረቱ ሶስት ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎችን እና አንድ የምርምር ተቋም ከምስራቅ አፍሪካ እንዲሁም አራት ታዋቂ የአውሮፓ የምርምር ተቋማት በመስክ ላይ የተመሰረተ ምርምር ጠንካራ ልምድ ያላቸው እና ሁለት የተከበሩ ለትርፍ ያልተቋቋሙ የምርት ልማት አጋሮች በ አር እና ዲ ውስጥ የተዘነጉ በሽታዎች ላይ የሚሰሩትን ያቀፈ ነው።
የአፍሪካዲያ ኮንሶርቲየም በአውሮፓ እና ባደጉ ሀገራት ክሊኒካል ሙከራዎች አጋርነት (ኢዲሲቲፒ) የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ነው። ይህ ፕሮጀክት በ ሆራይዞን 2020 ስር በአውሮፓ ህብረት የሚደገፈው የኢዲሲቲፒ2 ፕሮግራም አካል ነው፣ የምርምር እና ፈጠራ መዋቅር ፕሮግራም።
ስለ ዲኤንዲአይ
ለትርፍ ያልተቋቋመ የምርምር እና ልማት ድርጅት፣ ዲኤንዲአይ ችላ ለተባሉ ህሙማን፣ የቻጋስ በሽታ የያዛቸው፣ የእንቅልፍ ሕመም (የሰው አፍሪካዊ ትራይፓኖሶሚያሲስ)፣ ሊሽመናይሲስ፣ የፊላሪያል ኢንፌክሽ፣ ማይሴቶማ፣ የሕፃናት ኤችአይቪ እና ሄፓታይተስ ሲ አዳዲስ ሕክምናዎችን ለማቅረብ ይሰራል። ዲኤንዲአይ በአፍሪካ ከቀላል እስከ መካከለኛ ለሆኑ የኮቪድ-19 ጉዳዮች ህክምና ለማግኘት የአንቲኮቭ ክሊኒካዊ ሙከራን በማስተባበር ላይ ነው። እ.ኤ.አ. በ 2003 ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ፣ ዲኤንዲአይ እስከ አሁን አሥራ ሁለት አዳዲስ ሕክምናዎችን፣ ለካላዛር አዲስ ጣምራ መድኃኒትን ጨምሮ፣ ሁለት ቋሚ መድሀኒት መጠን ያለው ፀረ-ወባ እና ዲኤንዲአይ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 2018 ለሁለቱም የእንቅልፍ ሕመም ደረጃዎችን ለማከም የተፈቀደለት አዲስ የኬሚካል አካል ፌክሲኒዳዞል በተሳካ ሁኔታ ፈጥሯል። dndi.org
Media contact
ሊኔት ኦቲዬኖ (ዲኤንዲአይ፣ ናይሮቢ)
latieno@dndi.org
+254 705 639 909
ኢላን ሞስ (ዲኤንዲአይ፣ ኒውዮርክ)
imoss@dndi.org
+1 646 266 5216
Photo credit: Sydelle Willow Smith – EDCTP